ቀጥታ፡

አዲስ አበባ ስሟን መሆን የቻለችበት እጅግ ፈጣን፣ ሁለንተናዊ ለውጥ - ቃልን በተግባር!

አዲስ አበባን እንደ ስሟ ውብ ለማድረግ ባቀድነው መሠረት፣ በ24/7 የተለወጠ የሥራ ባሕል፣ በትጋት እና ታማኝነት ከተማችንን በሁሉም መስፈርቶች ለነዋሪዎቿ ምቹ እና ዓለም አቀፍ ተወዳዳሪነቷን የላቀ መዲና የማድረግ ሕልማችን በአስተማማኝ መንገድ ላይ ነው።

ከተማችን እየተገበረች ባለችው ሁለንተናዊ ልማት ለሁሉም የምትመች፣ ሁሉንም በፍትሀዊነት የምታገለግል ፣ ማንንም ያልዘነጋች የአካታች ልማት ማሳያ ከተማ እያደረግናት ነው።


 

ለሕፃናት፣ ለወጣቶች፣ ለአረጋውያንና ለአካል ጉዳተኞች፣ ለእግረኛው፣ ለባለ መኪናውና ለባለ ሳይክሉ የትራንስፖርት አማራጮችንና መሠረተ-ልማቶችን በፍትሐዊነት ያመቻቸች፤ ለስማርት ከተማነት፣ ለአገልግሎት አሰጣጥ፣ ለሸማቹ፣ ለባለሀብቱ ፣ ለንግድና ለኢንቨስትመንት ምቹ ሁኔታን የፈጠረች እና የኮፍረንስ ቱሪዚም ማዕከል ከተማ እየሆነች ነው።

ብዝሃ የምርት አቅርቦትን ለሸማቹ የሚያቀርቡ ተደራሽ የገበያ ማዕከላት፣ ሸማች ብቻ ሳይሆን አምራችም እየሆነች የመጣችበት እንዲሁም የትናንት ቀደምቶች ታሪክና አሸናፊነትን ከዛሬና ከነገ ጋር የሚያስተሳስሩ እንደ አድዋ ድል ሙዚየም፣ የአብረሆት የእውቀት መሸመቻ ማዕከል፣ አስደናቂ አረንጓዴ የሕዝብ መዝናኛ ስፍራዎችና የአደባባይ የኪነ-ጥበብ ትዕይንት ማቅረቢያዎችን አካትታ፤ የዲፕሎማሲ፣ የብዝሃ ማንነት፣ የብዝሃ ባህል ድምቀት እና የጠንካራ የአንድነት ማዕከል “አዲስ አበባ “የሁላችንም ከተማ ናት ።


 

በአሁኑ ወቅት አዲስ አበባን የኢትዮጵያ የብልጽግና ተምሳሌት ከማድረግ ባሻገር፣ የኢትዮጵያ ብልጽግና አይቀሬ መሆኑን በአዲስ አበባ ልማት በተግባር እያስመሰከርን እንገኛለን።

ከንቲባ አዳነች አቤቤ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም