ቀጥታ፡

የክልሉ ህዝብ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ለጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እውን መሆን የድርሻውን መወጣት አለበት

ባህር ዳር፤ መጋቢት 22/2018(ኢዜአ)፦ የአማራ ክልል ህዝብ የመራጭነት ካርድ በመያዝ ለጠንካራ ዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እውን መሆን የድርሻውን መወጣት አለበት ሲሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ ተናገሩ።

ርዕስ መስተዳድር አረጋ ከበደ፤ በሰባተኛው ጠቅላላ ምርጫ ለመራጭነት የሚያበቃቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

‎ርዕሰ መስተዳድሩ የምርጫ ካርዱን ከወሰዱ በኋላ እንደተናገሩት ጠቅላላ ምርጫው ሰላማዊ፣ ፍትሃዊና ዴሞክራሲያዊ እንዲሆን ሁሉም የድርሻውን ሊወጣ ይገባል።

በተለይም የክልሉ ህዝብ አስቀድሞ የምርጫ ካርድ በመውሰድ ለዴሞክራሲያዊ ስርዓት ግንባታ እውን መሆን የድርሻውን መወጣት አለበት ብለዋል።

በመሆኑም ዕድሜው ለመራጭነት የደረሰ የክልሉ ህዝብ ካርድ በመውሰድ ያመነበትን የፖለቲካ ፓርቲ መምረጥ የሚያስችለውን የምርጫ ካርድ መውሰድ እንዳለበት መልዕክት አስተላልፈዋል።


 

‎በብልፅግና ፓርቲ የአማራ ክልል ብልፅግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤት ኃላፊ ይርጋ ሲሳይም ለመራጭነት የሚያበቃቸውን የምርጫ ካርድ ወስደዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም