ቀጥታ፡

በምስራቅ ጎጃም ዞን ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ በመመደብ የገበያ ማረጋጋት ሥራ እየተከናወነ ነው

ደብረ ማርቆስ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ):-በምስራቅ ጎጃም ዞን ገበያውን ለማረጋጋት ከ169 ሚሊዮን ብር በላይ ተመድቦ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ የህብረት ሥራ ማስፋፊያ ተጠሪ ጽሕፈት ቤት አስታወቀ።

የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታረቀኝ ጀንበሬ እንደገለጹት፤ በበጀት ዓመቱ በዞኑ ለሚገኙ 22 የሸማች ማህበራት የፋይናንስ ድጋፍ በማድረግ የግብርናና የኢንዱስትሪ ምርቶች በተመጣጣኝ ዋጋ ለህብረተሰቡ እንዲቀርብ ተደርጓል። 

እስካሁን ባለው ሂደትም ከ580 ሺህ ሊትር በላይ የምግብ ዘይት፣ ከ800 ኩንታል በላይ የዳቦ ዱቄት፣ ከ4 ሺህ 500 ኩንታል በላይ ስኳር ለተጠቃሚው እንዲደርስ መደረጉን ገልጸዋል።

ጽሕፈት ቤቱ ለሚመጣው የትንሳኤ በዓል የዋጋ ንረትን ለመከላከል ዝግጅት እያደረገ መሆኑን ጠቁመው በዚህም ከ20 ሺህ ኩንታል በላይ ጤፍ፣ የዳቦ ዱቄት፣ ስኳርና ሽንኩርት በህብረት ስራ አማካኝነት ለገበያ ለማቅረብ እየተሠራ ይገኛል ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም