የአፋር ክልል የመስኖ ተፋሰስ ለዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሰነድ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ - ኢዜአ አማርኛ
የአፋር ክልል የመስኖ ተፋሰስ ለዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሰነድ ነው-ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 21/2018 (ኢዜአ)፦የአፋር ክልል የመስኖ ተፋሰስ ስራ ከዓመት እስከ ዝናብ አጠር ለሆኑ አካባቢዎች ትልቅ ትምህርት የሚሰጥ መሆኑን ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት፥በአዋሽ ወንዝ ተፋሰስ በመሥኖ እየለማ ያለው የሱፍ ምርት ለተሻገረ ግብርና እና ለተሻገረ ገጠር ራዕያችን ተደማሪ ሃብት ነው ብለዋል።
በክልሉ ዱብቲ ወረዳ የለማው የሱፍ ምርትም እንደቢጫው አበባ ተስፋን የሚያላብስ፤ እንደተሰበሰበው ምርት የተጨባጭ ብልጽግና አብነት መሆኑን ገልጸዋል።
በአፋር ክልል ያየነው በመሥኖ ተፋሰስ በረሃ የመሰለውን ምድር የምርት መትረፍረፊያ የማድረግ ትጋት ለሌሎችም በተለይም ከዓመት እስከ ዓመት ዝናብ አጠር አካባቢዎች ትልቅ የመማሪያ ሰነድ እንደሆነም ተናግረዋል።