ቀጥታ፡

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የ55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና አጠቃላይ አሸናፊ ሆነ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ)፦ ከመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ በአደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ሲካሄድ የቆየው 55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ተጠናቋል።

በሻምፒዮናው ላይ 36 ክለቦች፣ ተቋማት፣ 9 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የተሳተፉ ሲሆን፤ 621 ወንድ፣ 436 ሴት በድምሩ 1057 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል። 

 

ሻምፒዮናው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት የማበረታታት ዓላማ ያለው ነው።

በውድድሩ ማብቂያ ቀን 10 የፍጻሜ ውድድሮች ተካሄደዋል።

 

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሻምፒዮናው አጠቃላይ አሸናፊ በመሆን አጠናቋል።

መቻል ሁለተኛ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው መጨረሳቸውን የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በሻምፒዮናው መዝጊያ ላይ የተገኙት የአትሌቲክስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮማንደር ስለሺ ስህን እና ሌሎች የፌዴሬሽኑ ከፍተኛ አመራሮች ለክለቦች እና አትሌቶች የተዘጋጁ የገንዘብ፣ የዋንጫና ሜዳሊያ ሽልማቶችን አበርክተዋል።

ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ ለማካሄድ 10 ሚሊዮን ብር ወጪ ማድረጉን አስታውቋል።

 

ዘመናዊ የሰዓት መመዝገቢያ ማሽን (Time Tronics) በሻምፒዮናው ላይ ተግባራዊ ሆኗል።

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ፌዴሬሽኑ በየዓመቱ ከሚያካሂዳቸው ውድድሮች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀስ ነው።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም