ቀጥታ፡

55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጠናቀቃል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 20/2018 (ኢዜአ):- በአደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስታዲየም ከመጋቢት 15 ቀን 2018 ዓ.ም አንስቶ ሲካሄድ የቆየው 55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ፍጻሜውን ያገኛል።

በውድድሩ ላይ 36 ክለቦችና ተቋማት እና 9 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን 621 ወንድ፣ 436 ሴት በድምሩ 1057 ተወዳዳሪዎች ተሳትፈዋል። 

ሻምፒዮናው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ዓላማ በማድረግ ተከናውኗል።

ዘመናዊ የሰዓት መመዝገቢያ  ማሽን (Time Tronics) በሻምፒዮናው ላይ ተግባራዊ ሆኗል።

በሻምፒዮናው መዝጊያ ቀን 10 የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

ከፍጻሜ ውድድሮቹ መካከል በሁለቱም ጾታዎች የሚደረገው የ5000 ሺህ ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይጠበቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም