በክልሉ በስፖርት ዘርፍ የሚከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ - ኢዜአ አማርኛ
በክልሉ በስፖርት ዘርፍ የሚከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው ይቀጥላሉ -ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ በሐረሪ ክልል በስፖርት ዘርፍ የሚከናወኑ ውጤታማ ተግባራት ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ ገለጹ።
ርዕሰ መስተዳድር ኦርዲን በድሪ በክልሉ ነገ የሚጀመረው 23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል የዝግጅት ስራዎችን ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ እንዳሉት በክልሉ በስፖርቱ ዘርፍ የሚከናወኑ ስራዎች በተሻለ ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ጠቅሰው፤ በዘርፉ የሚከናወኑ ውጤታማ ተግባራትም ተጠናክረው እንደሚቀጥሉ አንስተዋል።
በተለይ በክልሉና በአካባቢው በተለያዩ የስፖርት ዘርፍ ክህሎት ያላቸው ታዳጊ ስፖርተኞችን የማፍራት ስራ በትኩረት መስራት ይገባል ነው ያሉት።
የሰርከስ ስፖርትን በማጎልበት በኩልም በሰፊው መስራት እንደሚገባ አስገንዝበዋል።
23ኛው ሀገር አቀፍ የባህል ስፖርቶች ውድድር እና 19ኛው የባህል ስፖርቶች ፌስቲቫል ከነገ ጀምሮ በሐረሪ ክልል ይካሄዳል።
ለአንድ ሳምንት የሚቆየው የባህል ስፖርቶች ውድድር እና ፌስቲቫል "የባህል ስፖርቶች ልማት ለኢትዮጵያ ከፍታ" በሚል መሪ ሀሳብ ይከናወናል።