ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ የፍልሰት አስተዳደርና አመራር ቁርጠኝነት በተሞክሮነት የሚወሰድ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018(ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ የፍልሰት አስተዳደርና አመራር ቁርጠኝነት በተምሳሌትነት የሚወሰድ መሆኑን በኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ገለጸ።

በድርጅቱ የፕሮግራም ኃላፊ ንላቡ ሳሻ ፓትሪክ ለኢዜአ እንዳሉት፤ የኢትዮጵያ መንግስት ብሔራዊ የፍልሰት አመራርና አስተዳደር ጠንካራ ቁርጠኝነት የፍልሰት ጉዳዮችን በውጤታማነት እያስተገበረ ነው።

የፍልሰተኞችንና የተቀባዩን ማህበረሰብ የልማት ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ኢትዮጵያ የምትወስዳቸው እርምጃዎች ለሌሎች ዓለማት ጭምር በአርዓያነት የሚወሰድ መሆኑን ገልጸዋል።

የኢትዮጵያ የፍልሰት አመራርና አስተዳደር ሥርዓትም ዓለም አቀፍ ስምምነቶችን መሰረት ያደረገና በቁልፍ ተሞክሮነት የሚጋራ እርምጃ እንደሆነ ተናግረዋል።

የኢትዮጵያ የፍልሰት አስተዳደርና አመራር ቁርጠኝነት በተምሳሌትነት የሚወሰድ ዓለም አቀፍ ተሞክሮ መሆኑንም አንስተዋል።

ከፍልሰት ጋር ተያያዥነት ያላቸው ጉዳዮች ላይ ያተኮረ የአምስት ዓመት ስትራቴጂ እ.እ.አ ከ2025 እስከ 2029 በኢትዮጵያ መንግስትና በዓለም አቀፉ የፍልሰት ድርጅት ተዘጋጀቶ ይፋ መደረጉን አስታውሰዋል።

ስትራቴጂክ ዕቅዱ ፍልሰተኞችንና ተቀባዩን ማህበረሰብ የጋራ ተጠቃሚነት በማረጋገጥ ሕጋዊና ደህንነቱ የተረጋገጠ የፍልሰት አስተዳደር ሥርዓት በመዘርጋት የመንግስትን ቁርጠኝነት እንደሚያሳይ አስረድተዋል።

የፍልሰተኞችን የህይወት ደህንነት በመጠበቅ ዘላቂ መፍትሔና ሕጋዊ የፍልሰት አስተዳደርና አመራር አማራጮች ላይ ትኩረት ማድረጉንም ጠቅሰዋል።

የስትራቴጂው መፍትሔ አመላካችም የፍልሰት አስተዳደርና አመራር የማህበረሰብ ጥበቃም የተጎጂዎችን ደኅንነት ለመጠቀም ጉልህ ሚና እንደሚጫወት አብራርተዋል።

ፍልሰተኞች ሕጋዊ የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ መሆናቸው በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ እንቅስቃሴዎቻቸው ላይ እክል እንዳይገጥማቸው በማድረግ ረገድ ገንቢ ሚና ይጫወታል ብለዋል።

የፍልሰተኞች ዲጂታል መታወቂያ ሥርዓቱ የኢትዮጵያ የሕግ ተገዥነትን በማፅናት ሕጋዊ የአስተዳደርና የአገልግሎት አሰጣጥ ተጠቃሚነት እንደሚያሰፍን ገልጸዋል።

በተለይም በኢትዮጵያ ድንበር አካባቢ የተጠለሉ ፍልሰኞች በሚኖራቸው አነስተኛ የንግድ እንቅስቃሴ ልክ ተጠቃሚነታቸውን በማሳደግ በገቢ ግብር አስተዳደር ላይ ከፍተኛ ጠቀሜታ እንደሚያበረክት ተናግረዋል።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም