ቀጥታ፡

የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓል እየተከበረ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018 (ኢዜአ)፦ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ምስረታ 50ኛ ዓመት የወርቅ እዮቤልዩ በዓል በተለያዩ መርሀ ግብሮች በመከበር ላይ ነው።

የምስረታ በዓሉ "በአዲስ ምዕራፍ ለተሻለ ነገ" በሚል መሪ ሀሳብ ነው እየተከበረ የሚገኘው።

በመርሀ ግብሩ የጠቅላይ ሚኒስትር ጽህፈት ቤት ኃላፊና የካቢኔ ጉዳዮች ሚኒስትር እና የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን የስራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ዓለምጸሐይ ጳውሎስ፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የመንግስት ልማት ድርጅቶች ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ መለስ መና፣ የከተማ እና መሰረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ፣ የፌዴራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ዋና ስራ አስፈጻሚ ረሻድ ከማል (ዶ/ር) እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ የመንግስት የስራ ኃላፊዎች እና ጥሪ የተደረገላቸው እንግዶች ታድመዋል።

በመርሀ ግብሩ በኮርፖሬሽኑ በተለያዩ አካባቢዎች የተገነቡ ህንጻዎችን አስመርቋል።

በዚህም ኮርፖሬሽኑ በፒያሳ ለወርቅ ንግድ ሱቆች አገልግሎት እንዲውል ተደርጎ የተገነባውን ዘመናዊ የንግድ ሕንፃ (ጎልድ ሞል) እና በአዲስ አበባ በተለምዶ ሱማሌ ተራ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ያስገነባውን ለመኖሪያ እና ለንግድ ቅይጥ ጥቅም የሚውለውን ባለ 27 ወለል ሕንፃውን አስመረቋል።


 

በተጨማሪም ሀገራዊ ለውጡን መነሻ አድርጎ ኮርፖሬሽኑ በተቋማዊ ሪፎርሙ ያስመዘገበውን ስኬት የሚያስቃኝ ኤግዚቢሽን ተከፍቷል።

ከኮርፖሬሽኑ ጋር አብሮ ለመሥራት ስምምነት ላይ የደረሱ የአውሮፓ የግንባታ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች በኤግዚቢሽኑ እየተሳተፉ ነው።

 

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም