የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅታቸውን ጀመሩ - ኢዜአ አማርኛ
የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅታቸውን ጀመሩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018 (ኢዜአ)፦ በቱርክዬ ለሚከናወነው የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር (Uefa) የወዳጅነት ዋንጫ ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾች ልምምድ ማድረግ ጀምረዋል።
በአሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ጥሪ የተደረገላቸው 22 ተጫዋቾች ሆቴል በመሰባሰብ ትናንት ቦሌ በሚገኘው ሩዋንዳ ሜዳ የመጀመሪያ ቀን ልምምዳቸውን መስራታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማህበር የሚያካሂደው የ’UEFA Frendship Cup’ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር በቱርክዬ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል።
በውድድሩ ላይ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ይሳተፋል።