ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል የልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ - ኢዜአ አማርኛ
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ በአፋር ክልል የልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 19/2018 (ኢዜአ)፦ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ እና የፌደራል መንግስት ከፍተኛ አመራሮች በአፋር ክልል የልማት ሥራዎችን ይመለከታሉ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ እና አመራሮቹ የልማት ስራዎችን ለመጎብኘት ዛሬ ማለዳ ሠመራ ሡልጣን ዓሊሚራህ ሐንፋሬ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱ የአፋር ክልል ርዕሰ መስተዳድር አወል አርባን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የሀገር ሽማግሌዎች እና የሠመራ ከተማ ነዋሪዎች ደማቅ አቀባበል አድርገውላቸዋል።