ኢትዮጵያ ወሳኝ ድል ተቀዳጀች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ ወሳኝ ድል ተቀዳጀች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ኢትዮጵያ ሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔን 3 ለ 0 አሸንፋለች።
ማምሻውን በሞሮኮ ኤል አብዲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ አቤል ያለው ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ከነዓን ማርክነህ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
ዋልያዎቹ ብልጫ ወስደው ተጫውተዋል። የማጥቃት እንቅስቃሴያቸው ጥሩ የሚባል ነበር።
ውጤቱን ተከትሎ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ድልድል የመግባት እድሏን አስፍታለች።
የሁለቱ ሀገራት የመልስ ጨዋታ መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም በድሬዳዋ ስታዲየም ይካሄዳል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በደርሶ መልስ ውጤት ካሸነፈ ወደ ምድብ ድልድል ማለፉን ያረጋግጣል።
የብሔራዊ ቡድኑ ዋና አሰልጣኝ ዮሐንስ ሳህሌ በመጀመሪያ ጨዋታቸው ድል ቀንቷቸዋል።
36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ እ.አ.አ ጁን 2027 በታንዛንያ፣ ኬንያ እና ዩጋንዳ ጣምራ አዘጋጅነት ይካሄዳል።