ቀጥታ፡

ለ2018/19 ለበልግ እና መኸር እርሻ የሚውል የአፈር ማዳበሪያ እየተሠራጨ ነው

ጅማ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡- 2018/19 ለበልግ እና ለመኸር እርሻ የሚውል 470 ሺህ ኩንታል የዳፕ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ እየተሠራጨ መሆኑን የጅማ ዞን ግብርና ጽሕፈት ቤት ኃላፊ ቲጃኒ ተማም ገለጹ።

በበልግ እና በመኸር እርሻ 880 ሺህ ሔክታር መሬት በዘር ለመሸፈን የመሬት ዝግጅት እየተደረገ መሆኑን ገልጸው፤ በዘር ከሚሸፈነውም ከ35 ሚሊየን ኩንታል በላይ ምርት ለማግኘት መታቀዱን ጠቁመዋል።


 

በዞኑ ምርትና ምርታማነትን ለማሳደግ አፈር ማዳበሪያ በኅብረት ሥራ ማኅበራት በኩል ለአርሶ አደሩ እየተሰራጨ መሆኑንም ለኢዜአ አረጋግጠዋል።

በዚህም መሠረት ለ2018/19 ለበልግ እና ለመኸር እርሻ የሚውል 920 ሺህ ኩንታል የአፈር ማዳበሪያ ለማቅረብ መታቀዱን ጠቅሰው፤ እስካሁን 470 ሺህ ኩንታል የዳፕ እና ዩሪያ ማዳበሪያ እየተሠራጨ መሆኑን ገልጸዋል።

ቀሪውም በአጭር ጊዜ እንደሚቀርብ አመላክተዋል።

በሌላ በኩል በ1 ሺህ 900 ሔክታር ላይ ምርጥ ዘር ተባዝቶ ለአርሶ አደሩ በጊዜ እንዲቀርብ እየተደረገ ነው ብለዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም