ቀጥታ፡

ለቀጣዩ የአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር የችግኝ ዝግጅት እየተከናወነ ነው    

ሆሳዕና፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡- በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል ለመጪው ክረምት የአረንጓዴ ሻራ መርሐ-ግብር የችግኝ ዝግጅት እየተከናወነ መሆኑን የክልሉ ደንና አካባቢ ጥበቃ ልማት ቢሮ አስታውቋል።


 

የቢሮው ኃላፊ አብርሃም መጫ ለኢዜአ እንደገለፁት፤ ባለፉት 7 ዓመታት በክልሉ 450 ሺህ ሔክታር በአካባቢ ጥበቃና በአረንጓዴ ዐሻራ መርሐ-ግብር ማልማት ተችሏል።


 

በዚህም የአፈር ለምነትን በማስጠበቅ፣ የግብርና ምርትና ምርታማነትን በማሳደግ የምግብ ዋስትናን ማረጋገጥን ጨምሮ በበርካታ ዘርፎች ተጨባጭ ውጤት ማስመዝገብ መቻሉን አብራርተዋል።

በዚህ ዓመትም 270 ሚሊየን የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸውን ችግኞች በመትከል 80 ሺህ ሔክታር መሬትን ለማልማት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየሠራን ነው ብለዋል።

ሥነ-ምኅዳርን መሠረት ያደረጉ ለምግብነትና ለሌሎች ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታ የሚውሉ ችግኞችን የማፍላትና የማዘጋጀቱ ተግባር እየተከናወነ እንደሚገኝም ነው ያረጋገጡት።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም