ቀጥታ፡

"ቪዚት ሐረር" የጎዳና ላይ የሩጫ ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ተካሄደ

ሐረር፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡- የሹዋሊድ በዓልን ምክንያት በማድረግ "ቪዚት ሐረር" የተሰኘ የጎዳና ላይ የሩጫ ፌስቲቫል በሐረር ከተማ ተካሂዷል።

የ5 ኪሎ ሜትር የጎዳና ላይ ሩጫ ፌስቲቫሉ፤ በርካታ የክልሉ ነዋሪዎች፣ አመራር አካላት፣ አትሌቶች፣ ታዳጊ ሕጻናት፣ ወጣቶችንና ሌሎችን አሳትፏል።

የጎዳና ላይ የሩጫ ፌስቲቫሉን ያስጀመሩት የክልሉ ሰላምና ፀጥታ አስተዳደር ቢሮ ኃላፊ ተውፊቅ መሀመድ እንዳሉት፤ የሩጫ ፌስቲቫሉ አብሮነትን የሚያጠናክር ነው።

የሐረሪ ክልል ስፖርት ኮሚሽን ኮሚሽነር ሙራድ አብዲ በበኩላቸው፤ የሹዋሊድ በዓልን በማስመልከት የተዘጋጀው የሩጫ ፌስቲቫል በሐረር የሚገኙ የመስኅብ ስፍራዎችን ለማስተዋወቅና እንዲጎበኙ ለማድረግ ታስቦ መዘጋጀቱን አስረድተዋል።
 
ይህም በክልሉ የሚገኙ ጥንታዊ፣ ባህላዊና ታሪካዊ የመስኅብ ስፍራዎችን ይበልጥ ለማስተዋወቅ ይረዳል  ብለዋል።
 
በፌስቲቫሉ አሸናፊ ለሆኑ ተወዳዳሪዎች የሜዳሊያና የዋንጫ ሽልማት ተበርክቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም