በምዕራብ ጎንደር ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 80 በርሜል ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ - ኢዜአ አማርኛ
በምዕራብ ጎንደር ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 80 በርሜል ነዳጅ በቁጥጥር ስር ዋለ
ገንዳውኃ፣ መጋቢት18/2018 (ኢዜአ):-በምዕራብ ጎንደር ዞን በህገ ወጥ መንገድ ሲጓጓዝ የነበረ 80 በርሜል ነዳጅ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አስታወቀ፡፡
ነዳጁን መያዝ የተቻለው በምእራብ አርማጭሆ ወረዳ በሁለት አይሱዙ ተሽከርካሪ ተጭኖ በመጓጓዝ ላይ እያለ ነው።
በዚህም ፖሊስ 80 በርሜል ነዳጅ ከሁለት ተጠርጣሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር በማዋል ምርመራ እያካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
ይህም በአቋራጭ ለመክበርና ለህገ ወጥ ዓላማ ለማዋል በማለም በሀገርና ህዝብ ላይ ተጨማሪ ጫና ለመፍጠር የተሞከረ ህገወጥ ተግባር መሆኑን የዞኑ ፖሊስ መምሪያ አዛዥ ኮማንደር ምስጋናው ካሴ አብራርተዋል።
እንደዚህ አይነት ወንጀሎችን ለመከላከል የፀጥታ አካላት ባደረጉት ጠንካራ ፍተሻና በህብረተሰቡ ጥቆማ መሰረት በህገወጥ መንገድ ሲዘዋወር የነበረው ነዳጅ መያዙን ተናግረዋል።