ቀጥታ፡

ከተማችን አዲስ አበባ ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ረገድ ተጨባጭ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች-ከንቲባ አዳነች አቤቤ

አዲስ አበባ፤መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፡-ከተማችን አዲስ አበባ ለችግር የተጋለጡ ነዋሪዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ረገድ ተባጭ ለውጥ እያስመዘገበች ትገኛለች ሲሉ ከንቲባ አዳነች አቤቤ ገለጹ።

ከንቲባዋ፥ ዛሬ ማለዳ በምግብ ዋስትና እና ብቃት የወጣቶች የሥራ ላይ ልምምድ ፕሮግራም 15 ሺህ 492 ተጠቃሚዎችን ከተረጂነት ወደ ምርታማነት በማሸጋገር አስመርቀናል ብለዋል።


 

ይህ ተግባር በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ(ዶ/ር)፥ ይፋ ከተደረጉት አምስቱ የ“ዜሮ ግቦች” መካከል አንዱና ዋነኛው የሆነው “ተረጂነትን እና ልመናን ዜሮ የማድረግ” ታላቅ ራዕይ በከተማችን ስኬታማ እየሆነ መምጣቱን ማሳያ ነው ያሉት።

ባለፉት አምስት ዓመታት በሴፍትኔት ፕሮግራም ውስጥ ተይዘው ሲረዱ የነበሩ ከ695 ሺህ በላይ ነዋሪዎችን ወደ ምርታማነት በማሸጋገር ራሳቸውን እንዲችሉና ቤተሰቦቻቸውን እንዲደግፉ ተደርጓል። 

በሌላ በኩል በከተማችን የሥራ ልምምድ ከተጀመረበት 2014 ዓ.ም ጀምሮ  ዛሬ የተመረቁትን 8 ሺህ 852 ወጣቶች ጨምሮ 49 ሺህ የሚሆኑ ዜጎች ከተረጂነት እና ስራ አጥነት ወጥተው  በተፈጠረላቸው ትስስር የሥራ ላይ ልምምድ  አጠናቀው ወደ ስራ ባለቤትነት እና አምራችነት  መሸጋገራቸውን ገልጸዋል።

#Ethiopian_News_Agency  #ኢዜአ

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም