ቀጥታ፡

ጃማይካ እና ቦሊቪያ ለዓለም ዋንጫ ጥሎ ማለፍ የፍጻሜ ጨዋታ አለፉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 18/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ የዓለም የክፍለ አህጉራት የግማሽ ፍጻሜ ጨዋታዎች በሜክሲኮ  ተካሄደዋል።

ዛሬ ማለዳ በአክሮን ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጃማይካ ኒው ካሌዶኒያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ባይሊ ካዳማርቴሪ በ18ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥሯል።

በጨዋታው ጃማይካ በኳስ ቁጥጥር እና የግብ እጅሎችን በመፍጠር ከተጋጣሚዋ ኒው ካሌዶኒያ ተሽላ ተገኝታለች።

ትናንት ከእኩለ ሌሊት በኋላ በተካሄደው ሌላኛው መርሐ ግብር ቦሊቪያ ሱሪናምን 2 1 ረታለች።


 

በቢቢቪኤ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሞሰስ ፓኒያጉአ በጨዋታ እና ሚጉዌል ቴርሴሮስ በፍጹም ቅጣት ምት የማሸነፊያ ጎሎቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሊያም ቫን ጌልደርን ለሱሪናም ብቸኛውን ግብ ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ጨዋታው ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።

ውጤቶቹን ተከትሎ ጃማይካ እና ቦሊቪያ ለዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ፍጻሜ አልፈዋል።

ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ ከጃማይካ እና ኢራቅ ቦሊቪያ ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ መጋቢት 18 ቀን 2018 ዓ.ም በሜክሲኮ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

በፊፋ የሀገራት የእግር ኳስ ደረጃ የተሻለ ደረጃ ያላቸው ዴሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ እና ኢራቅ አስቀድመው ለፍጻሜው ጨዋታ ማለፋቸው ይታወቃል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም