ቀጥታ፡

ቱርክዬ ወሳኝ ድል ተቀዳጅታለች

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ በ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአውሮፓ የጥሎ ማለፍ የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቱርክዬ ሮማንያን 1 ለ 0 አሸንፋለች።

ማምሻውን ኢስታንቡል በሚገኘው ቱርፓስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፌርዲ ካዲኦግሉ በ53ኛው ደቂቃ ብቸኛውን ጎል አስቆጥሯል።

በጨዋታው ቱርክዬ ብልጫ ወስዳ ተጫውታለች።

 

ውጤቱን ተከትሎ ቱርክዬ ወደ ጥሎ ማለፉ የመጨረሻ ማጣሪያ ጨዋታ አልፋለች።

ለዓለም ዋንጫ ለማለፍ ከስሎቫኪያ እና ኮሶቮ አሸናፊ ጋር መጋቢት 22 ቀን 2018 ዓ.ም ትጫወታለች።

የ23ኛው የፊፋ ዓለም ዋንጫ የአውሮፓ ጥሎ ማለፍ ቀሪ ጨዋታዎች ማምሻውን መካሄዳቸውን ይቀጥላሉ።

በጥሎ ማለፉ የሚያልፉ አራት ሀገራት አስቀድመው በቀጥታ ወደ ዓለም ዋንጫ ያለፉ 12 የአውሮፓ ሀገራትን ይቀላቀላሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም