ቀጥታ፡

ብሔራዊ ቡድኑ ከነገው ጨዋታ አስቀድሞ የመጨረሻ ልምምዱን አከናውኗል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ ኢትዮጵያ በ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንሲፔ ጋር ነገ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታውን ታደርጋለች።  

ብሔራዊ ቡድኑ ጨዋታው በሚደረግበት ኤል አብዲ ስታዲየም የመጨረሻ ልምምዱን ዛሬ ማምሻውን አከናውኗል። 

ሁሉም ተጫዋቾች በተሟላ ጤንነት ልምምዳቸውን ሰርተው ማጠናቀቃቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል። 

የኢትዮጵያ እና ሳኦቶሜ ጨዋታ ነገ ምሽት 12 ሰዓት ላይ በኤል ጀዲዳ ኤል አብዲ ስታዲየም ይከናወናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም