ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ቦሌ ክፍለ ከተማ ድል ቀንቶታል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ቦሌ ክፍለ ከተማ ባህር ዳር ከተማን 2 ለ 0 ረቷል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ምህረት በቀለ ሁለቱንም ግቦች አስቆጥራለች።

ምህረት አየለ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች። 


 

ከአራት ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሰው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ34 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል። በሊጉ ያሸነፋቸው ጨዋታዎች ብዛት ዘጠኝ ደርሰዋል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 15ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ባህር ዳር ከተማ በ16 ነጥብ 11ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም