ለዩኤፋ ፍሬንድሺፕ ካፕ ውድድር ለ22 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ - ኢዜአ አማርኛ
ለዩኤፋ ፍሬንድሺፕ ካፕ ውድድር ለ22 ተጫዋቾች ጥሪ ቀረበ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በቱርክዬ ለሚከናወነው የዩኤፋ ፍሬንድሺፕ ዋንጫ ውድድር አሰልጣኝ ቻለው ለሜቻ ለ22 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል።
ስመኝሽ ፍቃዱ (አዳማ ከተማ) እና ሊንጎ ኦማን (ቦሌ ክፍለ ከተማ) ጥሪ የተደረገላቸው ግብ ጠባቂዎች ናቸው።
በተከላካይ መስመር አሶሬ ሃይሶ (ባህር ዳር ከተማ )፣ ፍቅርአዲስ ገዛኸኝ ( ቦሌ ክፍለ ከተማ) ፣ ለምለም አስታጥቄ (ሃዋሳ ከተማ )፣ ሳባ ኃይለሚካኤል (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ቤተልሄም መስፍን (ሃዋሳ ከተማ)፣ ከአምላክነሽ ሃንኮ (ሃዋሳ ከተማ)፣ ዝናሽ ሰለሞን (ድሬዳዋ ከተማ) እና ወርቅነሽ ዘሪሁን (ሸገር ከተማ) ጥሪ ተደርጎላቸዋል።
ቱሪስት ቱንጋ (አዳማ ከተማ) ዙፋን ደፈርሻ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ሚለን ጋይም (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ ሜላት ጌታቸው (ቦሌ ክፍለ ከተማ)፣ ብርሃን ኃይለስላሴ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) እና ጋብሬላ አበበ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ) ቡድኑን እንዲቀላቀሉ ጥሪ ቀርቦላቸዋል።
ታሪኳ ጴጥሮስ (ሃዋሳ ከተማ)፣ ምትኬ ብርሃኑ (ሲዳማ ቡና)፣ ቤዛዊት ንጉሴ (መቻል) ፣ ህዳት ካሱ (ኢትዮ ኤሌክትሪክ)፣ ሊዲያ ኢያሱ (ጥሩነሽ ዲባባ አካዳሚ)፣ እና ማርያማዊት ታጠቅ (ኢትዮጵያ ስፖርት) በአጥቂ መስመር የሚገኙ ተጫዋቾች ናቸው።
የኢትዮጵያ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ልምምዱን ከዛሬ ጀምሮ እንደሚያደርግ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።
የአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር የሚያካሂደው የ’UEFA Frendship Cup’ ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ውድድር በቱርክዬ አስተናጋጅነት ከመጋቢት 28 እስከ ሚያዚያ 10 ቀን 2018 ዓ.ም ይከናወናል።
በዚህ ውድድር ላይ ከተለያዩ አህጉራት የተውጣጡ ሀገራት የሚሳተፉ ሲሆን የኢትየጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ከአውሮፓ እግር ኳስ ማኅበር ጋር በፈጠረው ግንኙነት ከአፍሪካ ከሚሳተፉ ሁለት ሀገራት መካከል አንዱ መሆን ችሏል።
በዚህም ከ18 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ይሳተፋል።
በዚህ ውድድር ላይ አስተናጋጇ ቱርክዬን ጨምሮ ኢትዮጵያ፣ ኖርዌይ፣ ኡዝቤኪስታን፣ ኮስታሪካ፣ ፓራጓይ፣ ዩራጓይ እና ሞሮኮ ተሳታፊ እንደሚሆኑ የተረጋገጡ ቡድኖች ናቸው