ቀጥታ፡

ይርጋጨፌ ቡና ከ12 ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦  በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ ግብር ይርጋጨፌ ቡና አዲስ አበባ ከተማን 4 ለ 2 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ መንደሪን ክንድይሁን ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር አዳነች አስፋው እና ፍጹም ብርሃኑ ቀሪዎቹን ጎሎች ለይርጋጨፌ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል። 

አለሚ በዬቻ እና መሰረት ምክረ ለአዲስ አበባ ከተማ ግቦቹን አስቆጥረዋል።


 

ሁለት ግቦችን ያስቆጠረችው መንደሪን ክንድይሁን የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች። 

ከ12 ጨዋታዎች በኋላ ወደ ድል የተመለሰው ይርጋጨፌ ቡና በ14 ነጥብ 11ኛ ደረጃን ይዟል። በውድድር ዓመቱ ሶስተኛ ድሉንም አስመዝግቧል።

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 16ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዲስ አበባ ከተማ በ11 ነጥብ 13ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም