የሀረሪ ክልል መንግስት ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ - ኢዜአ አማርኛ
የሀረሪ ክልል መንግስት ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላለፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦ የሀረሪ ክልል መንግስት ለሹዋሊድ በዓል የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።
የሕዝብን የአብሮነት ዕሴት ከሚያጎለብቱ ባህላዊ በዓላት አንዱ በክልሉ በየአመቱ በድምቀት የሚከበረው የሹዋሊድ በዓል እንደሚጠቀስ አመልክቷል።
የዘንድሮው የሹዋሊድ በዓል በክልሉ ኅብረ-ብሔራዊ አንድነትን በሚያሳይ መልኩ እና የክልሉን ልማት እና ዕድገት የበለጠ ማጠናከር በሚያስችል መልኩ በደማቅ ዝግጅት እንደሚከበርም ገልጿል።
ይህ ባህላዊ በዓል በክልሉ የመቻቻል፣ የአብሮነት እና የሰላም እሴትን በተለይም የቱሪዝም ዘርፉን በማጎልበት ረገድ ጠቀሜታው የጎላ መሆኑ ተመላክቷል።
የዘንድሮውን የሸዋሊድ በዓል በተሳካ መልኩ ለማክበር ሥራዎች ሲሰሩ መቆየታቸውን የገለጸው የክልሉ መንግስት፤ በአሁኑ ወቅትም በዓሉን ባማረና በደመቀ መልኩ ለማክበር አስፈላጊው የቅድመ ዝግጅት ተግባራት ሁሉ መጠናቀቃቸውን አስታውቋል።
በበዓሉ ላይም የሐረርን ታሪክ፣ እሴት እና ባህልን ሊያስተዋውቁ እና ሊገልጹ የሚችሉ ዝግጅቶችን በወንድማማችነት መንፈስ ለታዳሚው ይቀርባሉ።
የሀረሪ ክልል መንግስት የሹዋሊድ በዓል አብሮነትን፣ ሰላምንና ወንድማማችነት የሚጠናከርበት እንዲሆንም ተመኝቷል።