ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን ጀመረ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 17/2018 (ኢዜአ)፦  የኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን በሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ ማጣሪያ ከደቡብ ሱዳን ጋር ለሚያደርጋቸው የመጀመርያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች ዛሬ ልምምድ ማድረግ ጀምሯል።

ማለዳ ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ልምምድ በአሰልጣኝ ራውዳ ዓሊ ጥሪ ከተደረገላቸው 23 ተጫዋቾች መካከል 16ቱ መገኘታቸውን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።  


 

ቀሪዎቹ ተጫዋቾች ከዛሬ የክለብ ጨዋታዎች በኃላ ተጠቃለው ወደ ስብስቡ እንደሚገቡም አመልክቷል። 

10ኛው የፊፋ የሴቶች ከ17 ዓመት በታች ዓለም ዋንጫ በጥቅምት ወር 2019 ዓ.ም በሞሮኮ አስተናጋጅነት ይካሄዳል።

ኢትዮጵያ የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ጨዋታዋን በሚያዚያ ወር 2018 ዓ.ም ከደቡብ ሱዳን ጋር ታደርጋለች።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም