ቀጥታ፡

ኢትዮ ኤሌክትሪክ ወሳኝ ድል ተቀዳጅቷል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት ኢትዮ ኤሌክትሪክ ሲዳማ ቡናን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ህዳት ካሡ ግቦቹን አስቆጥራለች።

ግቦቹን ያስቆጠረችው ህዳት ካሡ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።


 

ከሁለት የአቻ ውጤቶች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ54 ነጥብ ከመሪው ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር በነጥብ እኩል በመሆን በግብ ክፍያ ተበልጦ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል።

በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ሶስት ነጥብ አግኝቷል። በሊጉ 17ኛ ድሉንም አስመዝግቧል። 

የሁለቱ ቡድኖች በነጥብ እኩል መሆን የዋንጫ ፉክክሩን የበለጠ ሳቢ አድርጎታል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ ዘጠነኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ሲዳማ ቡና በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ማሸነፍ አልቻለም።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ ጨዋታ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከመቻል ጋር አንድ አቻ ተለያይቷል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም