የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ - ኢዜአ አማርኛ
የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር የወንዝ ዳርቻ ልማት ሥራዎችን ጎበኙ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፡- የጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ጎበኙ።
የአዲስ አበባ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ አዳነች አቤቤ በማኅበራዊ ትሥሥር ገጻቸው ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከጣሊያን የውጭ ጉዳይና ዓለም አቀፍ ትብብር ምክትል ሚኒስትር ማሪያ ትሪፖዲ ጋር በመሆን ከእንጦጦ እስከ አራዳ ያለውን የወንዝ ዳርቻ ልማትና የአካባቢ ጥበቃ ሥራዎችን ጎብኝተናል ብለዋል።
ጉብኝቱ የተደረገው በአዲስ አበባ እየተካሄደ ከሚገኘው የመጀመሪያው የኢትዮ-ጣሊያን የኮንስትራክሽን፣ የመሠረተ-ልማትና የከተማ መልሶ ማልማት ፎረም ጎን ለጎን መሆኑንም አስታውቀዋል።
ለነበረን ፍሬያማ ጊዜም ማሪያ ትሪፖዲን አመሠግናለሁ ብለዋል ከንቲባዋ።