የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ጣለ - ኢዜአ አማርኛ
የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥብ ጣለ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ እና መቻል አንድ አቻ ተለያይተዋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ንግሥት በቀለ በ66ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ጎል ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ መሪ ሆኗል።
ጨዋታው በንግድ ባንክ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ሲባል ቱሪስት ለማ በ91ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ባሳረፈችው ግብ መቻል ወሳኝ አንድ ነጥብ አግኝቷል።
ለመቻል ግቡን ያስቆጠረችው ቱሪስት ለማ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ የሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ነጥቡን ወደ 54 ከፍ አድርጓል። ከተከታዩ ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ያለውን የነጥብ ልዩነት የማስፋት እድል አልተጠቀመበትም።
መቻል በ45 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ በሊጉ አምስተኛ ተከታታይ ድሉን የማስመዝገብ ሙከራው አልተሳካም።