ቀጥታ፡

የምስራቅ እዝ ተልዕኮውን በላቀ ብቃት እየተወጣ ነው -ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማ

ባህር ዳር፤ መጋቢት 16/2018 (ኢዜአ)፦ የምስራቅ እዝ የተሰጠውን ሕገ-መንግስታዊ ተልዕኮ በላቀ ብቃትና ጀግንነት እየተወጣ እንደሚገኝ የእዙ ዋና አዛዥ ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማ አረጋገጡ።

ሌተናል ጄነራል መሐመድ ተሰማ በቀጣናው ለተሰማሩ የዕዝ ኮማንድ፣ የኮር፣ የክፍለ ጦር እና የስታፍ መምሪያ አመራሮች የወቅታዊ ስምሪት አቅጣጫ ሰጥተዋል። 


 

ሌተናል ጄነራሉ በዚሁ ወቅት፤ ሠራዊቱ በአገሪቱ ላይ የተደቀኑ አደጋዎችን መመከት የሚያስችል ቁመና ላይ እንደሚገኝና የአመራር አካላትም ተቀናጅተው ሚናቸውን እየተወጡ መሆኑን ገልጸዋል።

የምስራቅ እዝም አገራዊና ተቋማዊ ተልዕኮውን በጽናት በመወጣት ላይ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአማራ ክልል እየተከናወኑ በሚገኙ ህግ የማስከበር ተግባራትም የባዕዳን ተልዕኮ አስፈፃሚ የሆኑ ኃይሎች ዓላማቸው እንዲመክን መደረጉን ጠቁመዋል። 

በቀጣይም ከክልሉ የፀጥታ ኃይሎችና ከሕዝብ ጋር ይበልጥ በመቀናጀት በቀጣናው አስተማማኝ ሰላም ለማስፈን በትኩረት እንደሚሰራ አስረድተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም