ቀጥታ፡

የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ መርሐ ግብር በሚያዝያ ወር ይካሄዳል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ዋንጫ የሩብ ፍጻሜ ጨዋታዎች ከሚያዝያ 14 እስከ 17 ቀን 2018 ዓ.ም  እንደሚካሄዱ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

በዚሁ መሰረት ቦዲቲ ከተማ ከመቀሌ 70 እንደርታ፣ ቤንች ማጂ ቡና ከኢትዮጵያ መድን፣ መቻል ከወልዋሎ አዲግራት ዩኒቨርሲቲ እና ነገሌ አርሲ ከሲዳማ ቡና ይጫወታሉ።

ጨዋታዎቹ በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደረጉ ፌዴሬሽኑ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም