ሃዋሳ ከተማ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ - ኢዜአ አማርኛ
ሃዋሳ ከተማ እና ሸገር ከተማ ነጥብ ተጋሩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ የ21ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር ሃዋሳ ከተማ እና ሸገር ከተማ ያለ ግብ አቻ ተለያይተዋል።
ጨዋታው የተካሄደው በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ነው።
የሸገር ከተማዋ ወርቅነሽ ዘሪሁን የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ሃዋሳ ከተማ በ43 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል። ሸገር ከተማ በ40 ነጥብ አምስተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል።
ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ21ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ልደታ ክፍለ ከተማ አዳማ ከተማን 4 ለ 1 አሸንፏል።