ቀጥታ፡

ልደታ ክፍለ ከተማ ወደ አሸናፊነት ተመልሷል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 21ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ልደታ ክፍለ ከተማ አዳማ ከተማን 4 ለ 1 አሸንፏል።

 

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ሰርካለም ሻፊ ሁለት ግቦችን ስታስቆጥር ይታገሱ ተገኘወርቅ እና እመቤት ፋንታሁን ቀሪዎቹን ጎሎች ለልደታ ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።

ሳሮን ካሳ ለአዳማ ከተማ ብቸኛውን ጎል አስቆጥራለች።

የልደታ ክፍለ ከተማዋ ይታገሱ ተገኘወርቅ የጨዋታው ኮከብ በመባል ተመርጣለች።


 

ከአራት የሊጉ ጨዋታዎች በኋላ ወደ አሸናፊነት የተመለሰው ልደታ ክፍለ ከተማ በ18 ነጥብ ደረጃውን ከ11ኛ ወደ 10ኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያስመዘገባቸውን ድሎች ብዛት አምስት አድርሷል።

በአንጻሩ በሊጉ 10ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው አዳማ ከተማ በ21 ነጥብ ዘጠነኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። ቡድኑ ባለፉት ሶስት ጨዋታዎች አላሸነፈም።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም