ጎንደር የኢትዮጵያ የልዕልና ምልክት፣ የሕብረ-ብሔራዊነት ማሳያና ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት እንደሰምና ወርቅ ያስማማች ልዩ ከተማ ናት - ኢዜአ አማርኛ
ጎንደር የኢትዮጵያ የልዕልና ምልክት፣ የሕብረ-ብሔራዊነት ማሳያና ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት እንደሰምና ወርቅ ያስማማች ልዩ ከተማ ናት
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018(ኢዜአ)፦ ጎንደር የኢትዮጵያ የልዕልና ምልክት፣ የሕብረ-ብሔራዊነት ማሳያና ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት እንደሰምና ወርቅ ያስማማች ልዩ ከተማ ናት ሲሉ ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ገለጹ።
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት የታሪክ ማህደር፣ የኪነ-ጥበብና የሥልጣኔ መፍለቂያ በሆነችው ታሪካዊቷ ጎንደር ከተማ ገብተናል ብለዋል።
ጎንደር የኢትዮጵያ የልዕልና ምልክት፣ የሕብረ-ብሔራዊነት ማሳያና ጥንታዊነትን ከዘመናዊነት እንደሰምና ወርቅ ያስማማች ልዩ ከተማ ናት ሲሉም በመልዕክታቸው ገልጸዋል።
በዐፄ ቴዎድሮስ ዓለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ለተደረገልን እጅግ ደማቅና ክብር የተሞላበት አቀባበል ለአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር፣ ለክልሉ ከፍተኛ አመራሮች፣ ለከተማዋ መስተዳድር የሥራ ኃላፊዎች፣ እንዲሁም "እንግዳ የእግዚአብሔር ነው" በሚለው ለጋስና አስተዋይ ማንነቱ ለታወቀው ኩሩው የጎንደር ሕዝብ ልባዊ ምስጋናዬን አቀርባለሁ ብለዋል።