ቀጥታ፡

የብሔራዊ ቡድኑ አምበል  ጋቶች ፓኖም ወደ ሞሮኮ አያመራም 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ)፦ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አምበል ጋቶች ፓኖም በወላጅ አባቱ ድንገተኛ ህልፈት ምክንያት ወደ ሞሮኮ ከሚጓዘው ልዑክ ሳይካተት መቅረቱን የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን አስታወቀ።

እግር ኳስ ፌዴሬሽንእና የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን አባላት በጋቶች ፓኖም ወላጅ አባት ህልፈት የተሰማቸውን ጥልቅ ሀዘን በመግለጽ ለተጫዋቹ እና ለቤተሰቡ መጽናናትን ተመኝተዋል።

ብሔራዊ ቡድኑ ከሳኦቶሜ እና ፕሪንስፔ ጋር ለሚያደርገው የ36ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የመጀመሪያ የቅድመ ማጣሪያ ጨዋታ ዛሬ ረፋድ ላይ ወደ ሞሮኮ ያቀናል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም