ቀጥታ፡

55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ዛሬ ይጀመራል

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 15/2018 (ኢዜአ):- 55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በአደይ አበባ ዓለም አቀፍ ስቴዲየም  ከዛሬ ጀምሮ ይካሄዳል።

ሻምፒዮናው ተተኪ አትሌቶችን ለማፍራት፣ ለአትሌቶች የውድድር እድል ለመፍጠር ፣ አትሌቶችን በሽልማት ለማበረታታት ዓላማ ያደረገ መሆኑን  የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ፌዴሬሽን አስታውቋል።

በውድድሩ ላይ 36 ክለቦችና ተቋማት እና 9 ክልሎችና ከተማ አስተዳደሮች የሚሳተፉ ሲሆን 621 ወንድ፣ 436 ሴት በድምሩ 1057 ተወዳዳሪዎች እንደሚሳተፉ አመልክቷል።

ፌዴሬሽኑ ለውድድሩ ማስኬጃ ከ10 ሚሊዮን ብር በላይ እንደመደበ አመልክቷል።

በሻምፒዮናው መክፈቻ የተለያዩ ውድድሮች ይካሄዳሉ።

በውድድሩ ላይ ዘመናዊ የሰዓት መቆጣጠሪያ ቴክኖሎጂ (Time Tronics) ተግባራዊ እንደሚሆንም ተመላክቷል።

55ኛው የኢትዮጵያ አትሌቲክስ ሻምፒዮና እስከ መጋቢት 20 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም