በደርቢው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አትሌቲኮ ማድሪድን አሸነፈ - ኢዜአ አማርኛ
በደርቢው ጨዋታ ሪያል ማድሪድ አትሌቲኮ ማድሪድን አሸነፈ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 14/2018 (ኢዜአ)፦ በስፔን ላሊጋ 29ኛ ሳምንት ተጠባቂ መርሐ ግብር ሪያል ማድሪድ አትሌቲኮ ማድሪድን 3 ለ 2 አሸንፏል።
በበርናባው ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ቪኒቨስ ጁኒየር በጨዋታ እና በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ግቦችን ሲያስቆጥር ፌዴሪኮ ቫልቬርዴ ቀሪዋን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።
አዴሞላ ሉክማን እና ናህኤል ሞሊና ለአትሌቲኮ ማድሪድ ግቦቹን አስቆጥረዋል።
ግብ ያስቆጠረው የሪያል ማድሪዱ ቬዴሪኮ ቫልቬርዴ በ77ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ቫልቬርዴ በወጣበት መንገድ የሪያል ማድሪድ ተጫዋቾች እና የአሰልጣኝ ቡድን አባላት ተቃውሟቸውን አሰምተዋል።
ተቃውሞው ከቢጫ ካርድ ያለፈ አያሰጥም የሚል ነው።
ጨዋታው አዝናኝ እና ተመጣጣኝ ፉክክር ተደርጎበታል።
አትሌቲኮ ማድሪድ ያገኘውን የቁጥር ብልጫ ወስዶ ተጭኖ ቢጫወትም ግብ ማስቆጠር አልቻለም።
242ኛው የማድሪድ ደርቢ በሪያል ማድሪድ አሸናፊነት ተጠናቋል።
ሁለት ግቦችን ያስቆጠረው ቪኒሸስ ጁኒየር የጨዋታው ኮከብ ሆኖ ተመርጧል።
በሊጉ 22ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሪያል ማድሪድ በ69 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃን ይዟል። ከሊጉ መሪ ባርሴሎና ያለውን የነጥብ ልዩነት ወደ አራት ዝቅ አድርጓል።
በዋንጫ ፉክክሩ ወሳኝ ነጥብ አግኝቷል።
በውድድር ዓመቱ ስድስተኛ ሽንፈቱን አትሌቲኮ ማድሪድ በ57 ነጥብ አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
የሪያል ማድሪዱ አሰልጣኝ አልቫሮ አርቤሎአ በመጀመሪያ የማድሪድ ደርቢ ድል ቀንቶታል።
በተያያዘም ዛሬ በተደረገ ሌላኛው ጨዋታ ባርሴሎና ራዮ ቫዮካኖን 1 ለ 0 በማሸነፍ በ73 ነጥብ መሪነቱን አጠናክሯል።