ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮናው ምንም ሜዳሊያ ሳታገኝ አጠናቀቀች - ኢዜአ አማርኛ
ኢትዮጵያ በዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮናው ምንም ሜዳሊያ ሳታገኝ አጠናቀቀች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በ21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ማምሻውን ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የተሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ተደርገዋል።
በ800 ሜትር ሴቶች ፍጻሜ አትሌት ንግስት ጌታቸው 1 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ከ73 ማይክሮ ሴኮንድ አራተኛ ወጥታለች።
የታላቁ ብሪታኒያ አትሌት ኬሊ ሆድግኪንሰን 1 ደቂቃ ከ55 ሴኮንድ ከ 30 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
በርቀቱ የዓመቱን ፈጣን ሰዓት አስመዝግባለች።
ስዊዘርላንዳዊቷ አውድሬይ ዌሮ ሁለተኛ እና አሜሪካዊቷ አዲሰን ዋይሊ ሶስተኛ ደረጃን ይዘው ውድድራቸውን አጠናቀዋል።
በሴቶችም የ1500 ሜትር የፍጻሜ ውድድር አትሌት ብርቄ ኃየሎም 4 ደቂቃ ከ01 ሴኮንድ ከ34 ማይክሮ ሴኮንድ አምስተኛ ወጥታለች።
የታላቋ ብሪታኒያ አትሌት ጆርጂያ ሀንተር ቤል 3 ደቂቃ ከ58 ሴኮንድ ከ53 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት የወርቅ ሜዳሊያ አግኝታለች።
አውስትራሊያዊቷ ጄሲካ ሁል ሁለተኛ ስትወጣ አሜሪካዊቷ ኒኪ ሂልትዝ ሶስተኛ ደረጃን ይዞ አጠናቃለች።
በሻምፒዮናው በስድስት አትሌቶች የተወከለችው ኢትዮጵያ ምንም ሜዳሊያ ሳታገኝ አጠናቃለች።