ቀጥታ፡

ማንችስተር ሲቲ ለዘጠነኛ ጊዜ የካራባኦ ዋንጫን አነሳ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ካራባኦ ካፕ ፍጻሜ ማንችስተር ሲቲ አርሰናልን 2 ለ 0 አሸንፏል።

 

ማምሻውን በዌምብሌይ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኒኮ ኦራይሊ በ60ኛው እና በ64ኛው ደቂቃ የማሸነፊያ ግቦቹን አስቆጥሯል።

 

ማንችስተር ሲቲ በሁለተኛው አጋማሽ ያሳየው የተሻለ እንቅስቃሴ ጨዋታውን እንዲያሸንፍ አድርጓታል።

 

አርሰናል በጨዋታው ግልጽ የግብ እድሎችን በበቂ ሁኔታ መፍጠር አልቻለም።

የእንግሊዝ ጠቅላይ ሚኒስትር እና የአርሰናል ደጋፊ የሆኑት ሰር ኪር ስታርመር ጨዋታውን በስታዲየም በመገኘት ተከታትለዋል።

 

ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ሲቲ ለዘጠነኛ ጊዜ የካራባኦ ዋንጫን አንስቷል። ሲቲ ከሊቨርፑል (10 ዋንጫ) ቀጥሎ የውድድሩ ስኬታማ ክለብ ነው።

ለአራት ዋንጫ የሚፎካከረው አርሰናል የመጀመሪያውን ዋንጫ አጥቷል።

 

ከ33 ዓመታት በኋላ የካራባኦ ዋንጫን የማሸነፍ ህልሙ አልተሳካም።

መድፈኞቹ ከዚህ ቀደም ውድድሩን ለሁለት ጊዜ አሸንፈዋል።

አርሰናል እና ማንችስተር ሲቲ በሊጉ አንደኛና ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም