ቀጥታ፡

አስቶንቪላ ወሳኝ ድል አሳክቷል

አዲስ አበባ ፤ መጋቢት 13/2018 (ኢዜአ)፡- በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት አስቶንቪላ ዌስትሃም ዩናይትድን 2 ለ 0 አሸንፏል።

በቪላ ፓርክ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ጆን ሚጊን እና ኦሊ ዋትኪንስ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አስቶንቪላ በ54 ነጥብ አራተኛ ደረጃን ይዟል። ሶስተኛ ደረጃ ላይ ከሚገኘው ማንችስተር ዩናይትድ ጋር የነጥብ ልዩነት ወደ አንድ ዝቅ አድርጓል።

በሻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፉክክር ወሳኝ ሶሶት ነጥብ አግኝቷል።

ዌስትሃም ዩናይትድ በ29 ነጥብ 18ኛ ደረጃን ይዞ ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛል።

በሌላኛው መርሐ ግብር ኖቲንግሃም ፎረስት ቶተንሃም ሆትስፐርስን 3 ለ 0 አሸንፏል።

በቶተንሃም ሆትስፐርስ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ኢጎር ጄሱስ፣ ሞርጋን ጊብስ ዋይት እና ታይዎ አዎኒ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

ኖቲንግሃም ፎረስት በ32 ነጥብ 16ኛ ደረጃን ይዟል።

ቶተንሃም ሆትስፐርስ በ30 ነጥብ 17ኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። የሰሜን ለንደኑ ቡድን የመውረድ ስጋቱ እየጨመረ ይገኛል።

በቲን ሳይድ ደርቢ ሰንደርላንድ ኒውካስትል ዩናይትድን 2 ለ 1 አሸንፏል።

ኬምስዳይን ታሊቢ እና ብሪያን ብሮቤይ ግቦቹን አስቆጥረዋል።

አንቶኒ ጎርደን ለኒውካስትል ብቸኛውን ጎል ከመረብ ላይ አሳርፏል።

ሰንደርላንድ በ43 ነጥብ 11ኛ፣ ኒውካስትል ዩናይትድ በ42 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዘዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም