ቀጥታ፡

መቻል አራተኛ ተከታታይ ድሉን አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት መርሐ-ግብር መቻል ቦሌ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል።

በአበበ በቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ትንቢት ሳሙኤል በ55ኛው ደቂቃ የማሸነፊያውን ጎል አስቆጥራለች።

የመቻሏ አጥቂ ሴናፍ ዋቁማ በ88ኛው ደቂቃ በሁለት ቢጫ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥታለች።

ገነት ዮሐንስ ከመቻል የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

በሊጉ አራተኛ ተከታታይ ድሉን ያስመዘገበው መቻል በ44 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። በውድድር ዓመቱ ያሸነነፈው ጨዋታ ብዛት 13 ደርሷል።

በውድድር ዓመቱ አምስተኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ቦሌ ክፍለ ከተማ በ31 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

ዛሬ አስቀድሞ በተደረገ የ20ኛ ሳምንት ጨዋታ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም