በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ - ኢዜአ አማርኛ
በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሲዳማ ቡና እና ድሬዳዋ ከተማ አቻ ተለያዩ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ሲዳማ እና ድሬዳዋ ከተማ ያደረጉት ጨዋታ አንድ አቻ ተጠናቋል።
በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ፊርማዬ ከበደ በ85ኛው ደቂቃ ባስቆጠረችው ጎል ድሬዳዋ ከተማ መሪ ሆኗል።
ጨዋታው በድሬዳዋ ከተማ አሸናፊነት ተጠናቀቀ ሲባል ኤልሳቤጥ ብርሃኑ በ93ኛው ደቂቃ ከመረብ ላይ ያሳረፈችው ግብ ለሲዳማ ቡና አንድ ነጥብ አስገኝቷል።
ለሲዳማ ቡና ግቡን ያስቆጠረችው ኤልሳቤጥ ብርሃኑ የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።
ውጤቱን ተከትሎ ሲዳማ ቡና በ28 ነጥብ ሰባተኛ ደረጃን ይዟል። ቡድኑ ሶስተኛ ተከታታይ ድሉን ማስመዝገብ አልቻለም።
ድሬዳዋ ከተማ በ21 ነጥብ ከነበረበት ዘጠነኛ ደረጃ ወደ ስምንተኛ ከፍ ብሏል። ቡድኑ ባለፉት አምስት የሊግ ጨዋታዎች አላሸነፈም።