ቀጥታ፡

በ800 ሜትር ሴቶች ማጣሪያ አትሌት ንግስት ጌታቸው ለፍጻሜ አለፈች 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና በፖላንድ ቶሩን ከተማ መካሄዱን ቀጥሏል።

በ800 ሜትር ሴቶች ግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ በምድብ ሁለት የተወዳደረችው አትሌት ንግስት ጌታቸው 1 ደቂቃ ከ59 ሴኮንድ ከ46 ማይክሮ ሴኮንድ ሁለተኛ በመውጣት ለፍጻሜ አልፋለች። 

በሶስት ምድብ በተካሄደው የማጣሪያ ውድድር ከየምድቡ አንደኛ እና ሁለተኛ የወጡ አትሌቶች ለፍጻሜ አልፈዋል። 

የፍጻሜው ውድድር ነገ ምሽት 3 ሰዓት ከ53 ላይ ይካሄዳል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም