በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ - ኢዜአ አማርኛ
በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና ኢትዮጵያውያን አትሌቶች የሚሳተፉባቸው የፍጻሜ ውድድሮች ይካሄዳሉ
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በፖላንድ እየተካሄደ የሚገኘው 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ ሁለተኛ ቀኑን ይዟል።
ምሽት 3 ሰዓት ከ4 ደቂቃ ላይ የሴቶች የ3000 ሜትር የፍጻሜ ውድድር ይካሄዳል።
ፍሬወይኒ ኃይሉ እና ባለሽኝ ባወቀ ኢትዮጵያን ወክለው ይወዳደራሉ።
በውድድሩ ላይ 15 አትሌቶች ይሳተፋሉ።
ምሽት 3 ሰዓት ከ22 ደቂቃ ላይ በሚካሄደው የ3000 ሜትር ወንዶች ፍጻሜ ጌትነት ዋለ እና አዲስ ይሁኔ የሚሳተፉ ይሆናል።
ከፍጻሜው ውድድር በተጨማሪ ከቀኑ 8 ሰዓት ከ22 በ800 ሜትር ግማሽ ፍጻሜ ማጣሪያ አትሌት ንግስት ጌታቸው ትወዳደራለች።
በሶስት ምድብ ተከፍሎ በሚደረገው ማጣሪያ ከእያንዳንዱ ምድብ አንደኛ እና ሁለተኛ የሚወጡ አትሌቶች ለፍጻሜው ያልፋሉ።