ቀጥታ፡

በማዕከሉ የተዘጋጀው የልዩ ትኩረት ዘርፍ ጋዜጠኝነት ሥልጠና ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለሥልጣን የልህቀት ማዕከል የተዘጋጀው የልዩ ትኩረት ዘርፍ ጋዜጠኝነት ሥልጠና ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ይገኛል።


 

"የሙያ ብቃት ለመገናኛ ብዙኃን ልህቀት" በሚል መሪ ሐሳብ በባለሥልጣኑ የልህቀት ማዕከል የተዘጋጀው የልዩ ትኩረት ዘርፍ ጋዜጠኝነት ሥልጠና ማጠናቀቂያ መርኃ ግብር እየተካሄደ ነው፡፡

ስልጠናው ለ21 ቀናት የተሰጠ ሲሆን 36 ጋዜጠኞች ስልጠናውን መከታተላቸውም ተጠቁሟል፡፡

በመርሃ ግብሩ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የዴሞክራሲ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አባላት፣ የብሔራዊ መረጃና ደኅንነት አገልግሎት ዳሬክተር ጀነራል እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን የቦርድ ሰብሳቢ አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን፣ የመንግሥት ኮሙኒኬሽን አገልግሎት ሚኒስትር ዴኤታ ከበደ ዴሲሳ እና የኢትዮጵያ መገናኛ ብዙኃን ባለስልጣን ዋና ዳይሬክተር ሃይማኖት ዘለቀ ተገኝተዋል።


 

ሥልጠናውን ተከታትለው ያጠናቀቁት የህዝብና የግል መገናኛ ብዙሃን ባለሙያዎችም ተገኝተዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም