በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1500 አትሌት በርቄ ሐየሎም ወደ ፍፃሜ አለፈች - ኢዜአ አማርኛ
በዓለም የቤት ውስጥ አትሌቲክስ ሻምፒዮና በ1500 አትሌት በርቄ ሐየሎም ወደ ፍፃሜ አለፈች
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018 (ኢዜአ)፦ 21ኛው የዓለም አትሌቲክስ የቤት ውስጥ ሻምፒዮና ዛሬ በፖላንድ ቶሩን ተጀምሯል።
በሴቶች 1500 ሜትር ማጣሪያ በምድብ ሁለት የተወዳደረችው አትሌት ብርቄ ሐየሎም 4 ደቂቃ 10 ሴኮንድ 66 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ ደረጃን በመያዝ ወደ ፍጻሜው አልፋለች።
የሴቶች 1500 ሜትር ፍጻሜ ከነገ በስቲያ ይካሄዳል።
በሴቶች 800 ሜትር ማጣሪያ በምድብ አራት ላይ የተወዳደረችው አትሌት ንግስት ጌታቸው በ2 ደቂቃ 02 ሴኮንድ 89 ማይክሮ ሴኮንድ አንደኛ በመውጣት ለግማሽ ፍፃሜ አልፋለች።
ኢትዮጵያ በሻምፒዮናው በስድስት አትሌቶች ተወክላለች።
ሻምፒዮናው እስከ መጋቢት 13 ቀን 2018 ዓ.ም ይቆያል።