ቀጥታ፡

በፕሪሚየር ሊጉ ሊቨርፑል ከብራይተን ቼልሲ ከኤቨርተን ይጫወታሉ

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12 /2018 (ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ 31ኛ ሳምንት የሁለተኛ ቀን ውሎ አራት ጨዋታዎች ይደረጋሉ።

ከቀኑ 9 ሰዓት ከ30 ላይ ብራይተን ሊቨርፑልን በአሜክስ ስታዲየም ያስተናግዳል።

ብራይተን በ40 ነጥብ 12ኛ ደረጃን ይዟል። ሊቨርፑል በ49ኝ ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

በ30ኛ ሳምንት ሰንደርላንድ 1 ለ 0 ያሸነፈው ብራይተን ተከታታይ ድሉን ለማስመዝገብ ይጫወታል። ሶስት ነጥብ በአውሮፓ መድረክ የመሳተፍ ተስፋውን ያለመልማል።

ባለፉት ሁለት ጨዋታዎች ያላሸነፈው ሊቨርፑል ማሸነፍ በአውሮፓ ሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርገው ፉክክር ወሳኝ ሶስት ነጥብ ያስገኝለታል።

 

በሌላኛው መርሐ ግብር ኤቨርተን ከቼልሲ ምሽት 2 ሰዓት ከ30 ላይ በሂል ዲኪንሰን ስታዲየም ጨዋታቸውን ያደርጋሉ።

ኤቨርተን በ43 ነጥብ ስምንተኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል። ቼልሲ በ48 ነጥብ ስድስተኛ ደረጃን ይዟል።

በ30ኛ ሳምንት ኤቨርተን በአርሰናል፣ ቼልሲ በኒውካስትል ዩናይትድ ሽንፈት አስተናግደዋል።

ሁለቱም ቡድኖች ወደ አሸናፊነት ለመመለስ ይፋለማሉ።
 

ሶስት ነጥብ ለኤቨርተን በአውሮፓ መድረክ፣ ቼልሲ በሻምፒዮንስ ሊግ ለመሳተፍ በሚያደርጉት ፉክክር ወሳኝ የሚባል ነው።

ፉልሃም ከበርንሌይ ምሽት 12 ሰዓት እና ሊድስ ዩናይትድ ከብሬንትፎርድ ምሽት አምስት  ሰዓት ላይ ይጫወታሉ።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም