ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሏል - ኢዜአ አማርኛ
ማንችስተር ዩናይትድ ነጥብ ጥሏል
አዲስ አበባ፤ መጋቢት 12/ 2018(ኢዜአ)፦ በእንግሊዝ ፕሪሚየር ሊግ የ31ኛ ሳምንት የመጀመሪያ መርሐ ግብር ቦርንማውዝ እና ማንችስተር ዩናይትድ ሁለት አቻ ተለያይተዋል።
በቫይታላቲ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ ራያን ክሪስቲ በጨዋታ እና ጁኒየር ክሩፒ በፍጹም ቅጣት ምት ለቦርንማውዝ ግቦቹን ከመረብ ላይ አሳርፈዋል።
ብሩኖ ፈርናንዴዝ በፍጹም ቅጣት ምት እና የቦርንማውዙ ጀምስ ሂል በራሱ ላይ ለዩናይትድ ጎሎቹን አስቆጥረዋል።
የማንችስተር ዩናይትዱ ተከላካይ ሃሪ ማጓየር በ78ኛው ደቂቃ በቀይ ካርድ ከሜዳ ወጥቷል።
ጨዋታው ተመጣጣኝ እና አዝናኝ ፉክክር ተደርጎበታል።
ማጥቃት ላይ ያተኮረው የሁለቱ ቡድኖች ጨዋታ በርካታ የግብ እድሎች ተፈጥረውበታል።
ውጤቱን ተከትሎ ማንችስተር ዩናይትድ በ55 ነጥብ ሶስተኛ ደረጃን ይዟል።
በሻምፒዮንስ ሊግ ፉክክሩ ወሳኝ ነጥብ ጥሏል።
ቦርንማውዝ በ42 ነጥብ 10ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።