ቀጥታ፡

በሴቶች ፕሪሚየር ሊግ ሸገር ከተማ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ነጥብ ተጋሩ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት ሸገር ከተማ እና  ኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ አቻ ተለያይተዋል።

በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው ጨዋታ ማርታ ወልዴ በ23ኛው ደቂቃ ላይ ከመረብ ላይ ባሳረፈችው ግብ ሸገር ከተማ መሪ ሆኗል።

የሸገር ከተማዋ ማህሌት ምትኩ በ90ኛው ደቂቃ ላይ በራሷ ላይ ያስቆጠረችው ጎል ለኢትዮ ኤሌክትሪክ አንድ ነጥብ አስገኝቷል።   


 

የኢትዮ ኤሌክትሪኳ ቤተልሄም በቀለ በጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።

ውጤቱን ተከትሎ ሸገር ከተማ በ39 ነጥብ አምስተኛ ደረጃን ይዟል።

ኢትዮ ኤሌክትሪክ በ51 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ይገኛል። 

ባለፉት ሁለት ተከታታይ የሊጉ ጨዋታዎች ነጥብ የጣለው ኢትዮ ኤሌክትሪክ ከሊጉ መሪ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ያለው የነጥብ ልዩነት ወደ ሁለት ከፍ ብሏል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም