ቀጥታ፡

ሃዋሳ ከተማ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ ያደረገበት ድል አስመዘገበ 

አዲስ አበባ፤ መጋቢት 11/2018 (ኢዜአ)፦ በኢትዮጵያ ሴቶች ፕሪሚየር ሊግ 20ኛ ሳምንት የመጀመሪያ ጨዋታ ሃዋሳ ከተማ ልደታ ክፍለ ከተማን 1 ለ 0 አሸንፏል። 

ረፋድ ላይ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተካሄደው ጨዋታ፤ ሥራ ይርዳው በ62ኛው ደቂቃ ብቸኛውን ግብ አስቆጥራለች።

ግቡን ያስቆጠረችው ሥራ ይርዳው የጨዋታው ኮከብ ሆና ተመርጣለች።


 

በሊጉ 12ኛ ድሉን ያስመዘገበው ሃዋሳ ከተማ በ42 ነጥብ ደረጃውን ከአራተኛ ወደ ሶስተኛ ከፍ አድርጓል። 

በአንጻሩ በውድድር ዓመቱ 13ኛ ሽንፈቱን ያስተናገደው ልደታ ክፍለ ከተማ በ15 ነጥብ 10ኛ ደረጃን ይዟል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም