ቀጥታ፡

በክልሉ የተገኘውን ሰላምና ልማት በማስቀጠል የመረዳዳት ባህልን ማዳበር ይገባል - ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ

ጅግጅጋ፤ መጋቢት 11/2018(ኢዜአ)፦ በሶማሌ ክልል የተገኘውን ሰላምና ልማት በማስቀጠል የመረዳዳት ባህልን ማዳበር እንደሚገባ የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ ተናገሩ።

በዓሉ ምዕመናን፣ የሃይማኖት አባቶች፣ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ነዋሪዎች በተገኙበት በተለያዩ ሃይማኖታዊ ሥርዓቶች ተከብሯል።

የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር ሙስጠፌ ሙሐመድ በበዓሉ ላይ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ባስተላለፉበት ወቅት፤ በረመዳን ወር ስናከናውነው የነበረውን መልካም ተግባር ልናስቀጥል ይገባል ብለዋል።


 

በክልሉ የተገኘውን ሰላምና ልማት በማስቀጠል የመረዳዳት ባህልን ማዳበር እንደሚገባም አስገንዝበዋል።

የሶማሌ ክልል እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት ሼክ አህመድ መሐመድ እንደገለጹት፤ ሙስሊሙ ማኅበረሰብ በአንድነትና በመተባበር የልማት ሥራዎችን ማስቀጠል አለበት ብለዋል።

በክልሉ የሰፈነውን ሰላም በመጠበቅና የተቸገሩ ወገኖችን በመርዳት በዓሉን ማሳለፍ እንደሚገባ አስገንዝበዋል።

የኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት
2015
ዓ.ም